አሥር ከፍተኛ የደርግ ባለሥልጣናት ይፈታሉ

9 Jun

በዘር ማጥፋት ወንጀል ከተከሰሱት 23 ከፍተኛ የደርግ ባለሥልጣናት መካከል 20 ዓመት የታሠሩት አሥር ከፍተኛ የደርግ ባለሥልጣናት ይፈታሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ባለፈው ሳምንት 23ቱ ባለሥልጣናት የተፈረደባቸው የሞት ፍርድ በፕሬዚዳንት ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ ወደ ዕድሜ ልክ ዝቅ መደረጉን ተከትሎ፣ ታስረው 20 ዓመት የሞላቸው ባለሥልጣናት እንደሚለቀቁ ታውቋል፡፡

ቀሪዎቹም ባለሥልጣናት 20 ዓመት እንደሞላቸው ጊዜያቸውን ጠብቀው ይለቀቃሉ፡፡ ከ23ቱ መካከል በደርግ ዘመን የደኅንነት ሚኒስትር የነበሩት ኮሎኔል ተስፋዬ ወልደ ሥላሴ ግንቦት 27 ቀን 2003 ዓ.ም. ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩ መሆኑ ይታወሳል፡፡

አሥሩ ባለሥልጣናት ከማረሚያ ቤቱ ሰባት ገጽ ያለው ቅጽ ወስደው እንደሞሉ ምንጮች ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ የአዲስ አበባ ማረሚያ ቤቶች ምክትል ዳይሬክተር አቶ አብርሃም ወልዳረጋይ ለዋልታ እንደገለጹት፣ ባለሥልጣናቱ በማረሚያ ቤት ቆይታቸው ብዙ ተምረዋል፡፡ ባለሥልጣናቱ ከኅብረተሰቡ ጋር አብሮ የመኖር ችግር እንደማይገጥማቸው አክለው ገልጸዋል፡፡

አሁን በእስር ላይ የሚገኙት ባለሥልጣናት ሻምበል ፍቅረ ሥላሴ ወግደረስ፣ ሻምበል ለገሰ አስፋው፣ ሻለቃ መላኩ ተፈራ፣ አቶ አብዱልቃድር መሐመድ፣ ጄኔራል ለገሠ በላይነህ፣ አቶ ገስግስ ገብረ መስቀል፣ መቶ አለቃ ጴጥሮስ ገብሬ፣ መቶ አለቃ ስለሺ መንገሻ፣ ኮሎኔል ናደው ዘካሪያስ፣ ሻምበል በጋሻው አታላይ፣ ሜጀር ጄኔራል ውብሸት ደሴ፣ ኮሎኔል ፍስሐ ደስታ፣ ኮሎኔል እንዳለ ተሰማ፣ ኮሎኔል ደበላ ዲንሳ፣ መቶ አለቃ አርጋው ይመር፣ ሻለቃ ደጀኔ ወንድማገኘሁ፣ አቶ እሸቱ ሸንቁጤ፣ ሻምበል ገሠሠ ወልደ ኪዳን፣ መቶ አለቃ ደሳለኝ በላይ፣ ወታደር ልሳኑ ሞላ፣ ወታደር አበበ እሸቱና ወታደር ዘሪሁን ማሞ ናቸው፡፡

Ethiopian Reporter

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: