ከዚህም ፤ ከዚያ፤

12 Mar

For Amharic PDF: Click here

ምንድነው፤ ከዚህም ከዚያ አትሉኝም??? አንዱን ሳነሳ አንዱን ስጥል፤፤ ስለ ማሞ ውድነህ ፤ ብዬ የጀመርኩት ነገር አገራዊ ይዘት ቢይዝብኝ ፤ ሰፋ አድርጌ ፤ ከዚህም ከዚያ አደረኩት፤፤
ማሞን ሳስብ በህሊናዬ ቀድሞ የሚመጣው የኤርትራ ጉዳይ ነው፤፤ የኤርትራ ጉዳይ፤ ሲታሰብ ደግሞ፤ ፊት ለፊት ድቅን የሚሉት ጥቂት መፃህፍት ናቸው፤፤ ስለ ኤርትራ ጉዳይ በቀዳሚነት የማሞ ውድነህ መፅሃፍን የሚቀድም መፅሀፍ ያለ አይመስለኝም ፤ ሌሎቹ ደግሞ፤ የበአሉ ግርማ፤ ኦሮማይ እና ፤ የ ዘውዴ ረታ፤የኤርትራ ጉዳይ፤ መፅህፍት ጥቂቶቹ ናቸው፤፤ የዘውዴ ረታ አባት ፤የንግስት ዘውዲቱ ባለሟልና ፀሀፊ የነበሩ በመሆናቸው ጭምር የግብአት /RESOUCE/ ችግር አይታይባቸውም ፡፡
የማሞ ውድነህን፤ የኤርትራ ጉዳይ፤ መፅሀፍ ለየት የሚያደርገው፤ ለረጅም ዓመታት ፤ በ1960ዎቹ በኤርትራ (የቀድሞ የኢትዮጲያ ክፍለ-ሃገር) የመንግስት ፕሬስ ክፍል ሃላፊ ሆነው በሰሩባቸው አመታት፤ በኤርትራ ጉዳይ ላይ በቀጥታ የሚመለከታቸውን ከፍተኛ ሰዎች (ጃንሆይን ጭምር)፤ ከበዓሉ ግርማ፤ኦሮማይ ይልቅ ፤አብሮ ሰርቶና በግንባር አግኝቶ መወያየት መቻላቸው ይመስለኛል፤፤ ለንፅፅር ያህል ከወሰድነው፤ በዓሉ ግርማ፤ እንደ ቀይ ኮከብ ዘመቻ፤ የቡድን አባል ሆኖ ያዘጋጀው ኦሮማይ፤ የፍቅር ትእይንት (፤አባቴ ይሙት ደደብ ነህ፤) ፤ ከመግባቱ በቀር፤ ከዘመቻው የስራ ሪፖርት ላይ መቀዳቱን፤ ለምን በዓሉን ገደላችሁት ሲባሉ ደርጎች የሚሰጡት ማስተባበያ እንደሆነ ቀጥሏል ፤፤ ይመስለኛል; ኮረኔል መንግስቱም፤ በትግላችን ውስጥ፤ የቀይ ኮከብ ዘመቻን ያላካተቱት፤ አንድም ቀድሞ የተቀዳ ስራ መሆኑን በመገንዘብ ላለመድገም ወይንም በቅፅ 2 አዘናግተውን ሊመለሱበት ፈልገውም ይሆናል፤፤ እንዲያው ለጨዋታችን አነሳነው እንጂ እሳቸውማ(ኮረኔል) ምን ያልደገሙት(ያልቀዱት) ነገር አለና፤፤ የአክሱማውያን ስልጣኔ፤ ፤ የኢማም መሃመድ ግራኝ ወረራ እና፤ ከዛጉዌ ስርወ መንግስት በኋላ የመጡ ስርወ መንግስታት የጠበቃቸው ስራና ፈተና፤ወዘተ፤ ወዘተ…. መንግስቱ ከ 17 ዓመት በኋላ እረፍት ሲያገኙ ያነበቧቸው ይሆኑ እንዴ…ሲል አንዱ፤ በሆነ ጋዜጣ ላይ አስተያየቱን ፅፎ አይቻለሁ፤፤
ካነሳነው አይቀር፤ ኮረኔል፤ እራሳቸውን፤ እንደጃንሆይ ደጋግመው፤ እኛ ሲሉ አስተውዬ፤ አይ፤ ብቻቸውን አለመሆናቸውን ለማስገንዘብ ፈልገው ነው የሚል ግምት ይዜ ነበር፤፤ አይ….አይ …አይደለም፤፤ ብቻቸውን ፤ንግግር ሲያደርጉ በሚያሳይ ፎቶ ግርጌ ስር፤ ስለ ሶማሊያ ጦርነት መግለጫ ስንሰጥ ፤የሚሉ ሃረጎች ሳይ ፤ በፈዛዛ የሚታለፍ ጉዳይ አለመሆኑ ገብቶኛል፤፤ ሌላው ደግሞ፤ ፕሮፌሰር መስፍንን በተደጋጋሚ ፤ ዶክተር መስፍን ወልደማሪያም ይላሉ፤፤ እርግጥ ነው ፤ ፕሮፌሰር መስፍን፤ የፃፉት አይደለም፤ እግረመንገዳቸውን ያወሩት ለ PHD መመረቂያ Thesis ሊሆናቸው ይችላል፤፤ ማንስ ደፍሮ ሊያስተምራቸው?? መምህሩ(ምናባዊው መምህር) በንዴት፤ ጭቅጭቅ ነው? ትምህርት? ብሎ ጥሎዋቸው እንደሚሄድ ግን ይታየኛል፤፤
ወደ ማሞ ስንመለስ፤
ማሞን በቀረበው ጊዜ ደግሞ፤ ከአክሱም አስመላሽ ኮሚቴ ጋርም አስታውሳቸዋለሁ፤፤ ስለ አክሱም ሀውልት ደግሞ ማንሳታችን ካልቀረ፤ ኢህአዲግ የሰራው የትግል ፍሬ እየመሰለን ብዙዎቻችን፤ ድጋፍም ባንሰጥ፤ ዝምታ ላይ ማተኮራችንን አስተውያለሁ፤፤ በጣልያን ሀገር ይገኝ የነበረውን የአክሱም ሃውልት ፤ ወደ ሃገሩ መመለሱ ታሪካዊ ፋይዳው ላቅ ያለ እንደሆነ እኔም የገባኝ፤ ጆን ስፔንሰር፤ ወደ ሃገሩ አለመመለሱን፤ የኢትዮጲያዊያን ድክመት እንደሆነ ፤በጥርስ የገባች አገር / Ethiopia at Bay / መፅሃፋቸው ላይ አፅንኦት ሰጥተው መፃፋቸውን በማንበቤ ይመስለኛል፤፤ አቶ መለስ በተደገጋጋሚ ፈረንጅ አያዋጣችሁምም……. ቢሉም አንዳንዶቻችን ግን ከፈረንጅ ካልሰማን አናምንምና፤፤
ማሞ ያልረገጡት መሬት፤ ያላዩት ዳገት ፤ ያልወረዱበት ቁልቁለት የለም ማለት ይቻላል፤፤በስለላ መፅኃፍት ላይ ማተኮራቸውም፤ ምክንያታዊ እንደሆነ ማሞ ሲያስረዱ፤ /ሀገሬ ከውጭ ጥቃት እራሷን ለመከላከል፤ ሌሎች አለማት የደረሱበትን የስለላ ታሪኮች፤ እኔም የገባኝን ያህል እንድታውቅ በመፈለጌ ነው/ ይላሉ ፤፤የስለላ ገሃዳዊ ትእይንቶችንም በራሳቸው ላይ እንዳዩም ሲያሳዩን፤፤ ለምሳሌም፤ የሻቢያው፤ ኢሳያስ አፈወርቂ ታዋቂ ሽፍታ ከመሆኑ በፊት ፤ ከጀብሃ፤ እና ከመንግስት ጋር እየተመላለሰ Double Agent /የሁለቱ አለም ሰላይ/ በመሆን ሲያገለግል እንደነበር በአንድ ወቅት ከማሞ አንብቤያለሁ፤፤ በተያያዘ ዘገባም ፤ ጀብሃ፤ ማሞ የሚወዱትን ጥሬ ስጋ ቤት አጥንቶ የግድያ ሙከራም ቃጥቶባቸውም እንደነበረና፤ በእሳቸው ዳፋ ሌላው መግባቱን እንዲሁ ፤፤
ማሞ ፤ ሰው አይነኩም፤ ከነኳቸውም ወይም እንደሚነኳቸው ከጠረጠሩም አይለቁም፤፤ በአንድ ወቅት ፤ የትምህርት ሚኒስትራችን ፤ አጤ ኃይለስላሴ፤ ሲሆኑ ፤ ምክትላቸው እንዲሆኑ ደግሞ የፈቀዱላቸው፤ ክቡር ከበደ ሚካኤል ነበሩ አሉ፤፤ ከበደ ሚካኤል በወቅቱ አገሪቱ ከገባችበት የእውቀት አዘቅት ለማውጣት ከሚታትሩ ምሁራን መካከል አንዱ ነበሩም አሉ፤፤ ማሞ እና ከበደ ሚካኤልም አይመቻቹም ይባላልም ነበረ፤፤ ማሞ ከተመቻቸው በግልጥ ፤ በጋዜጣ ላይ ከበደ ሚካኤል፤ ከሰው ከመቅዳት ውጪ ምን አዲስ ነገር አላቸውስ ብለው ይሞግቱም ነበር፤፤ ከበደ ሚካኤል አፍልቀው መፃፍ እንደማይሆንላቸውም በመግለፅ፤፤ ማሞም በኋላው ላይ እንደ ከበደ ሚካኤል ወደ ትርጉም ስረው ላይ ጠቅለው ገቡበት እንጂ፤፤

ሰው ወደ ላይ ወጣ
መልሶም ወረደ
ቁልቁለት ሳይገታው
የሰው ልጅ ወረደ – ወረደ ነጐደ
አቀበት የወጣው
ጉልበቱ ደከመ – ሕይወቱ በረደ፡፡- ማሞ ውድነህ

ነብስ ይማር፤
Jonas Jontambek

Advertisements

ለዲሞክራሲ እና ለመልካም አስተዳደር ገፅታ ግንባታ፤ ምርጫ ቦርድ በመድረክ የባንክ ሂሳብ ውስጥ 3,598 ብር አስቀመጠ፤፤

12 Mar

ኢሕአዴግ የሀገሪቱን ሀብት በብቸኝነት ጠቅልሎ መያዙ አልበቃ ብሎታል – መድረክ
የተመድ የልማት ፕሮግራም የሰጠውን ገንዘብ ኢሕአዴግ ወዳጅ እየገዛበት ነው – አቶ ገብሩ አሥራት


ኢሕአዴግ እንደ ገዢ ፓርቲ፣ እንደ መንግሥትና እንደ ነጋዴ፤ የሀገሪቱን ሀብት በብቸኝነት ጠቅልሎ መያዙ አልበቃ ብሎት፣ በዴሞክራይታዜሽን ስም ከለጋሽ ሀገሮች ወይም ከመንግሥት ካዝና በፖለቲካ ፓርቲዎች ድጋፍ ስም የሚመጣውን ገንዘብ ጠቅልሎ መውሰዱ ሳያንሰው ለአጋሮቹና ለታማኝ ተቃዋሚዎቹ በመስጠት፣ ወዳጅ እንዲገዛበት መፈቀዱ፣ ኢሕአዴግንም ሆነ ቦርዱን በኢትዮጵያ ሕዝብ እና በታሪክ ፊት የሚያስጠይቅ ድርጊት መሆኑን መድረክ ገለፀ፡፡ በጉዳዩ ዙሪያ ያነጋገርናቸው የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ (መድረክ) የስራ አስፈጻሚ አቶ ገብሩ አስራት፤ ቦርዱ ለአምስቱ ፓርቲዎች ስላከፋፈለው ገንዘብ ለአዲስ አድማስ እንደገለፁት፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለ2004 ዓ.ም፣ ለፖለቲካ ፓርቲዎች የዕለት ተግባር ማከናወኛ፣ 10 ሚሊዮን ብር ማስፈቀዱንና 7.5ሚ ብር ለኢህአዴግ እንደተሰጠ ተናግረዋል፡፡ “የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት” በሚል ለተቋቋሙት አምስት ፓርቲዎች “ከኢሕአዴግ ድርሻ የተቆነጠረ ነው” ተብሎ፣ 1 ሚሊዮን ብር እንደተከፋፈለ ተናግረዋል፡፡
ቦርዱ ለዚህ የሰጠው ምክንያት ደግሞ ገንዘቡን ፓርቲዎቹ ለ2002 ዓ.ም ምርጫ ባቀረቧቸው ዕጩዎች ብዛት መሰረት ሲያከፋፍል፣ ከኢሕአዴግ ቀጥሎ ከፍተኛ ዕጩዎችን ለ2002 ዓ.ም ምርጫ አቅርቦ ውጤቱን ለተቀማው የስድስት ፖለቲካ ፓርቲዎች ድርጅት ስብስብ ለሆነው መድረክ ግን ምንም ገንዘብ አለመስጠቱን ተናግረዋል፡፡
የአትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በመድረክ የባንክ ሂሳብ ቁጥር ስላስገባው 3598 ብር እና ለፖለቲካ ፓርቲዎች የዕለት ተግባር ማከናወኛ ከመንግሥት ካስፈቀደው 10 ሚሊዮን ብር ላይ በአንድ መቀመጫ አስልቶ ስላስገባለት ገንዘብ በሚመለከት ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በጻፈው ደብዳቤ፤ “አምና ለተመሳሳይ ተግባሮች ማከናወኛ ተብሎ ያለ ፍላጐታችን በባንክ ሂሳብ ቁጥራችን ገቢ ያደረጋችሁትን 3698.41 ብር፣ ክፍፍሉ ኢፍትሃዊና አድሎአዊ ሆኖ በማግኘታችን በመልሶ መለኪያ ተጨማሪ ወጪ አውጥተን ለቦርዱ ተመላሽ ማድረጋችን እየታወቀ፣ ለ2004 ዓ.ም በጀት ዓመትም ያችው ብር 3598.41 ያለ ፍላጐታችን በባንክ ሂሳባችን ገቢ መደረጉና ይህንንም ገንዘብ ገቢ ከተደረገልን የድጋፍ ገንዘብ፣ ከሦስት እጥፍ በላይ ወጪ አውጥተን፣ የውጭ ኦዲተር ቀጥረን፣ በኦዲተር የተረጋገጠ የፋይናንስ ሂሳብ ሪፖርት እንድናቀርብ መጠየቃችን ተገቢ አይደለም” በማለት ተቃውሞውን አሰምቷል፡፡
ፓርቲው ያለፍላጐቱ በባንክ የሂሳብ ቁጥሩ የገባውን ገንዘብ አምና እንዳደረገው ሁሉ ለቦርዱ ተመላሽ ማድረጉን በደብዳቤ ጠቅሶ፤ ለወደፊትም ቢሆን የድጋፍ ገንዘቡ ክፍፍል አፈፃፀም ከአድሎአዊነት እስካልፀዳ ድረስ፣ ቦርዱ በመድረኩ የባንክ ሂሳብ ቁጥር ገቢ ማድረጉን እንዲያቆም በደብዳቤ ጠይቀውታል፡፡ ከዚህ በኋላ ግን ቦርዱ ያለ መድረክ ፍላጐት፣ በባንክ ሂሳብ ቁጥር፣ ገንዘቡን ገቢ ቢያደርግ፤ መድረክ ገንዘቡን ለመመለስ ወይም ደግሞ ገቢ ከተደረገው ገንዘብ እጥፍ በላይ ወጪ አውጥቶ እና ኦዲተር ሾሞ፣ የፋይናንስ አጠቃቀምን ሪፖርት ለማቅረብ የማይገደድ መሆኑን ለቦርዱ በደብዳቤ አስታውቋል፡
1 ሚሊዮን ብሩ ተከፋፍሎ የተሰጣቸው የጋራ ምክር ቤት አባላቱ የኢትዮጵያ ራዕይ ፓርቲ (ኢራፓ)፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ንቅናቄ (መኢብን)፣ የኢትዮጵያ ፍትህና ዲሞክራሲያዊ ኃይሎች ግንባር (ኢፍዴኃግ)፣ የኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኤዴፓ) እና የኢትዮጵያ ሰላምና ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢሰዴፓ) አምና በወጣው መስፈርት መሠረት ለሁሉም ፓርቲዎች እኩል የሚከፋፈል 20 በመቶ፣ በ2002 ዓ.ም ምርጫ ወቅት ባቀረቡት ዕጩ ብዛት 60 በመቶና በዚሁ ምርጫ ወቅት ባቀረቡት የሴት ዕጩ 20 በመቶ ድርሻ እንዲከፋፈል በመደረጉ፣ ፓርቲዎች ተቃውመው እንደነበር ይታወሳል፡፡ ስለ ጉዳዩ አስተያየታቸውን የሰጡት አቶ ገብሩ፤ “ገንዘብ መስጠቱ የሚያመጣው ለውጥ የለም፡፡ ኢሕአዴግ ለእነዚህ ፓርቲዎች ገንዘብ እየሸለማቸው እና ወዳጅ እየገዛበት ነው፡፡ ይህ ደግሞ ሙስና ነው፡፡” ብለዋል፡፡
Addis Admas.

Al-Amoudi, The Black Billionair for 2012

9 Mar

Nigerian billionaire Aliko Dangoteis no longer the richest black person in the world. He’s been ousted by Ethiopian-born Saudi billionaire Sheikh Mohammed Al-Amoudi who is worth an estimated $12.5 billion. That’s $1.3 billion richer than Dangote. American TV mogul Oprah Winfrey remains the only black female billionaire in the world.
Of the 1,226 people who made it to the 2012 FORBES list of the world billionaires, only 6 are black.
Mohammed Al-Amoudi, $12.5 billion Saudi Arabia. Oil
Born to a Saudi father and Ethiopian mother, Mohammed Al-Amoudi immigrated to Saudi Arabia as a child where he made a fortune handling lucrative construction contracts for the Saudi Royal family. He subsequently invested in Sweden, Morocco and Ethiopia. His most prominent assets include oil companies Svenska Petroleum Exploration, which produces crude oil in Africa, and refinery operator Preem. Al-Amoudi stays committed to the country of his birth: Ethiopia. In February, he announced a $3.4 billion investment in Ethiopia via his newly formed Derba conglomerate. The funds will be invested in agriculture, cement production, steel and transport. He also owns gold mines in the country and the very prestigious 5-star Sheraton Hotel, Addis. Passionate soccer fan.

Other Black Billionaries:

Aliko Dangote, $11.2 billion

Mike Adenuga, $4.3 billion
Patrice Motsepe, $2.7 billion
Oprah Winfrey, $2.7 billion
Mo Ibrahim, $1.1 billion

Forbes.

Yemen’s Saleh is in Ethiopia, foreign ministry says

25 Feb

Ethiopia’s foreign ministry spokesman says the outgoing president of Yemen is in the east African country.

Dina Mufti said Friday that Ali Abdullah Saleh arrived in Ethiopia Thursday night. Mufti said he “doubts” Saleh will fly on to Yemen.

Yemen on Tuesday voted to replace Saleh with Vice President Abed Rabo Mansour Hadi, who is expected to be sworn in Saturday. He takes over after months of uncertainty over whether Saleh would step down in the face of popular protests that plunged Yemen into crisis.

Before arriving in Ethiopia, Saleh spent more than three weeks in the U.S. for medical treatment from wounds sustained in a June assassination attempt. The 69-year-old Saleh, Yemen’s ruler for 33 years, has pledged to attend his successor’s inauguration.
Associated Press

10 Million Birr Financial Support Given to Political Parties

22 Feb

The National Electoral Board of Ethiopia (NEBE) said it has made financial assistance to political parties, which have seats in federal and regional parliaments.

Public Relations and Coordination Head with NEBE, Yeshi Fekade told ENA over the weekend that the Board has provided a 10 million Birr financial support to the political parties in 2004 EC for doing their day-to-day activities.

Yeshi said the board provided the money to the political parties from government budget in accordance with the amended proclamation on the registration of political parties.

The money was provided to 10 political parties, she said, adding, the amount of money which each party gets depends on the number of seats each party has in the parliaments.

The money was deposited in the bank accounts of the respective parties.

The financial support is aimed at helping the political parties to develop the awareness of the public in politics and introduce the aims of their respective political parties to the public thereby enhance the active participation of the public in political activities.

EPRDF, the Somali People Democratic Party, the Benishangul-Gumuz People Democratic Party, the Afar National Democratic Party and the Gambella Peoples Unity Democratic Movement are included among the parties which received the finacial assistance.

According to ENA, the Harari National League, the Argoba People Democratic Organization, Forum for Demiocratic Dialogue in Ethiopia-Medrek, the Coalition for Unity and Democracy and the All Ethiopian Unity Organization are also included.

According to Yeshi, 10 million Birr financial support was also provided to political parties in 2003 EC.

Walta

የባለቤቱን አይኖች በስለት የወጋው አመለጠ

20 Feb

ሁለቱም አይኖቿ ለጊዜው አያዩም

የ24 ዓመቷ ፀዳለች አስረስ ለቤተሰቦቿ 12ተኛ ልጅ ስትሆን ከአሁኑ ባለቤቷ ጋር የምትታወቀው ገና ከልጅነቷ ጊዜ ጀምሮ ነበር፡፡ ፀዳለችና የ26 ዓመቱ መሰለ ግርማ የአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን እዛው ቡሬ አብረው የተማሩ ሲሆን ሁለቱም ዩኒቨርስቲ የሚያስገባ ነጥብ በማምጣታቸው ፀዳለች አምቦ ዩኒቨርስቲ ስትገባ መሰለ ጅማ ዩኒቨርስቲ ተመደበ፡፡ መለያየታቸው ያላስደሰተው መሰለ፤ ባቀረበው ሃሳብም ፀዳለች እንደምንም ብላ እሱ ወዳለበት ዩኒቨርስቲ እንደተቀየረች ትናገራለች፡፡

የዩኒቨርስቲ ትምህርታቸውን አንድ ላይ መከታተል ከጀመሩ በኋላ ግን ፀዳለች ውጥረት ውስጥ እንደገባች ታስታውሳለች፡፡ ከሌሎች ተማሪዎች ጋር የነበራትን ቀረቤታና ግንኙነት ያልወደደው ፍቅረኛዋ፤ ክፉኛ ይጨቀጭቃትና ያስጠነቅቃት እንደነበር ፀዳለች ተናግራለች፡፡የዩኒቨርስቲ ትምህርታቸውን በ2001 ዓ.ም የጨረሱት ሁለቱ ወጣቶች በዳሸን ባንክ የተለያዩ ቅርንጫፎች ሥራ የተቀጠሩ ሲሆን ወዲያው ትዳር መስርተው ሴት ልጅ ወልደዋል፡፡ ትዳር ከመሰረቱ በኋላ ጭቅጭቁና ማስፈራሪያው መባባሱን የገለፀችው ወጣቷ፤ የምለብሰውን ልብስ የሚመርጠው እንኳን እሱ ነበር – ትላለች፡፡ ወደ ስራ ስትሄድም መተጣጠብና መቀባባት እንደማይፈቅድላት እንዲሁም ፀጉሯን እንደነገሩ እንድታስይዝ ብቻ እንደሚያስገድዳት ተናግራለች፡፡ ፀዳለች በጐፋ ዳሸን ባንክ፣ ባለቤቷ መሰለ ደግሞ በቄራ ዳሸን ባንክ ቅርንጫፍ መ/ቤቶች እንደሚሰሩ የተናገረችው ወጣቷ፤ መ/ቤት ስትሄድ የምትለብሳቸውን ልብሶች በተመለከተ “አለባበስሽን አስተካክይ” የሚል ተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያና ማስፈራሪያ ይሰጣት እንደነበር ጠቁማለች፡፡ “አንቺ ብትለይኝ የእህትና የወንድሞችሽን ልጆች ት/ቤታቸው ሄጄ እገድላለሁ፤ አይንሽን ጐልጉዬ አወጣለሁ” በሚል ዘወትር ያስፈራራት እንደነበርም ፀዳለች ተናግራለች፡፡ በየወሩ የምታገኘውን ደሞዝ አንድም ሳታስቀር ለባሏ ታስረክብ የነበረችው ወጣቷ፤ የትራንስፖርት ብቻ ቆርጦ ይሰጠኝ ነበር ብላለች፡፡ የቤት አስቤዛ ሸምታ እንደማታውቅ ገልፃ፤ ሸመታውን የሚያከናውነው ባለቤቷ እንደነበር ተናግራለች፡፡

የዘወትር ፀባቸው መነሻ ቅናት እንደነበር የምትናገረው ፀዳለች፤ ሞባይል ቢኖረኝም ከእሱ ስልክ ውጪ ማንሳትም ሆነ መደወል እንደትችል ገልፃለች፡፡ በምትሰራበት የዳሸን ባንክ ጐዳ ቅርንጫፍ በየወሩ የስራ ልውውጥ እንደሚደረግ የምትናገረው ፀዳለች፤ ጥር 28 ቀን 2004 ዓ.ም ከቀድሞው ዳታ ወደ ኮምፒውተር የማስገባት ሥራዋ ተቀይራ ካውንተር ላይ በቴለርነት እንድትሰራ ከአለቃዋ ትዕዛዝ እንደደረሳት ጠቁማ ጉዳዩን ለባለቤቷ ስታማክረው ግን መብሸቁን ገልፃለች፡፡ “በመስታወት ውስጥ ሆነሽ ለመታየት ነው“ በሚል የቅናት ስሜት ተቃውሞውን በመግለጽ ካውንተር ላይ አልሰራም ብላ ለአለቆቿ እንድትነግራቸው ከፍተኛ ማስጠንቀቂያ ሰጣት፡፡በነጋታው ከስራ ወጥታ አስራ አንድ ሰዓት ተኩል ገደማ ቤቷ የደረሰችው ፀዳለች፤ መጀመሪያ ያገኘችው ባለቤቷን ነበር፡፡ የሁለት አመት ልጃቸውን አቅፎ የነበረው መሰለ፤ ልጁን ለሠራተኛው ይሰጥና ልጅቷን እንደያዘች አቮካዶ ገዝታ እንድትመጣ ሠራተኛዋን ያዛታል፡፡ የቤት ሠራተኛዋም ህፃኗን አቅፋ ትወጣለች፡፡ ሠራተኛዋ እግሯ እንደወጣ መሰለ ለሚስቱ ጥያቄ ያቀርባል “ያልኩሽን ለአለቃሽ ነገርሽ? ፀዳለችም፤ “ዋናው አለቃዬ ባለጉዳይ ስለበዛበት ለምክትሉ ነግሬው በተመደብሽበት ቦታ መስራት አለብሽ ብሎኛል” በማለት መልስ ሰጠች፡፡ ባለቤቷም በቁጣ ስሜት “እንዴት በዛሬ ቀን ባለጉዳይ በዛ!” ይልና በቦክስ ይላታል፡፡ የተለመደው ድብደባ ነው ብላ አስባ ነበር፡፡ ድብደባው እያየለ ሲመጣ ግን ከወትሮው የከፋ መሆኑን ተገነዘብኩ ትላለች፡፡ በሰነዘረባት ተደጋጋሚ ቦክሱ አይኖቿ እንዳበጡ የምትናገረው ወጣቷ፤ ስለት ይዞ እንደተጠጋት ገልፃለች፡፡ ራሷን ለመከላከል መታገል ጀመረች፡፡ የሷ ትግል ግን ባለቤቷ ያሰበውን ከመፈፀም አላገደውም፡፡ ጡቷንና እጇን ከነከሳትና ደጋግሞ በቦክስ ከመታት በኋላ አይኗን በስለቱ ወግቷታል፡፡ በደረሰባት ጥቃት ብዙ ደም እንደፈሰሳት የገለፀችው ፀዳለች፤ ራሷን ስታ እንደነበርና የነቃችው በላንድማርክ ሆስፒታል ውስጥ እንደሆነ ትናገራለች፡፡ ባሏ ጉዳቱን ካደረሰ በኋላ የሞተች መስሎት ጥሏት ጠፍቷል፡፡ እስከትላንት ድረስም አልተያዘም ብላለች – ተጐጂዋ፡፡ በተሰነዘረባት ተደጋጋሚ ቦክስ የአፍንጫዋ አጥንት በመሰበሩ ከፍተኛ ደም በአፍና በአፍንጫዋ እየፈሰሰ ሲሆን የህክምና ባለሙያዎች ሊረዷት እንዳልቻሉ ተናግራለች፡፡

ዓይኗ ከፍተኛ እብጠት ስላለው ሃኪሞች የጉዳት መጠኑን ለማወቅ እንዳልቻሉም ጠቁማ፤ ከአንድ ሳምንት በኋላ እንድትመለስ ተነግሯት ወደ ቤቷ መመለሷን ገልፃለች፡፡ በወንድሟ ቤት ተኝታ ጉዳትዋን ስታስታምም የቆየችው ፀዳለች፤ በአፍንጫዋ የሚፈሰው ደም ባለመቆሙ ትላንት ገርጂ ወደሚገኘው ካዲስኮ ጠቅላላ ሆስፒታል መወሰዷን ቤተሰቦቿ ለአዲስ አድማስ ገልፀዋል፡፡ በአሁኑ ሰዓት የተጐጂዋ ሁለቱም ዓይኖች ማየት እንደማይችሉ ታውቋል፡፡ “ነጭ ነገር ብቻ ነው የሚታየኝ” ብላለች – ፀዳለች፡፡

Addis Admas

Andualem was beaten Up.

18 Feb

Yesterday, around noon time, I received information that Andualem was beaten up by an inmate in his prison cell by an inmate day before yesterday and that someone should come to the prison and see him. I phoned his brother and his lawyers to ask them if they could
visit him in the afternoon. They could not go to the prison in the afternoon because the visit hours were only in the mornings.

They could see him today and came to UDJ office to report what they found out. First of all about Andualem’s condition. Andualem, who is usually emotionally and spiritually strong, was down. He was depressed and was weeping when he met his brother and his lawyers. He complained of headache. A small bruise can be seen on his face on the right side below his eye. He expressed that he has fear that “they” want to kill him. No medical care has been given to Andualem so far.

Background: Andulem is in a prison cell for 14 people in the so called maximum security zone (Zone 3) with people such as Ato Bekele Gerba of OFDM and Olbana Lelisa of OPC and Dr. Tilahun Fantahun. The cell does not have windows.

About a month ago a prisoner named Ibas Asfaw was added to Andualem’s cell. Ibas has been in prison for 16 years and was once sentenced to death because of murder. His sentence was latter changed to life imprisonment. It is said that he has transmittable illness. Ibas is
provocative, insulting and quarrelsome. He takes away food from his cell inmates by force and gives it away to others. He is frequent visitor to the office of prison administration and is said that he is in friendly relations with the authorities there.

Ibas started insulting Andualem since the 13th of February. He took away papers Andualem was using to writ his defense case for the court in two weeks. No one knows where he took the papers. On the 14th, Ibas comes to the cell at around 13 hours with another prisoner
from outside the cell and closes the door and asks Bekele and Dr. Tilahun, who were resting, telling them to get out of the room because they have something secret to talk with Andualem. The two refused to get out. Ibas then went directly to Andualem and kicked him on the left side of his head. Andualem fall down. Ibas boxed Andualem three times while he lay unconscious on the cement floor. Bekele was trying to push away Ibas while Dr. Tilahun called the guards. The guards took Ibas away.

It is rumored that he was taken to the prison administration office and received more than Bir 2,300 and taken to another cell in zone 1. It is said that he receives money since 2005 because he was injured during the shooting in prison when many prisoners are said to have
been killed.

To the questions of the lawyers the prison authorities said that they can allocate prisoners in any cell they want, that this is administrative matter, they will deal with Ibas administratively, they can get Andualem’s papers from Ibas and Andualem can forward appeal and accusation to the prison administration if he wants to. The prison administration did not take the matter seriously.

Conclusion: We suspect that the placing of Ibas in Andualem’s cell is deliberate and that it was an indirect way of torturing Andualem, humiliate him and have him morally, psychologically and physically broken down, as has been done to Burtukan Mideksa.

The Executive Committee of UDJ will discuss on the matter tomorrow and will decide what action it would take. In the mean time I appeal to all friends to forward this information to all defenders of the Human Rights to condemn what happened to Andualem and demand that he gets medical attention as soon as possible.

Dr. Negaso Gidada, Chairman of Unity for Democracy and Justice Party

Photo of a naked Ethiopian woman caused a storm

15 Feb

A picture of a nude Ethiopian woman caused a storm after it was posted to Facebook by an Israeli photojournalist and documentarian.
Disgusted viewers posted remarks slamming the photographer, Ziv Koren, accusing him of taking advantage of the woman – a new immigrant – who pictured bathing in a mikve at a Jewish agency camp. Internet surfers questioned whether the photographer asked the woman for permission to take and publish the photo, and said the authenticity of any consent would be questionable, given her vulnerable status at the time it was taken.
“That woman probably doesn’t know Hebrew, and whoever translated surely didn’t explain that it was artistic photography and that she should feel free to refuse,” wrote one Internet surfer, adding that “it must be understood what’s going on with the Falashmura [immigrants], they are passed on the message in simplistic words or hints, that if they refuse to participate in the religious ceremonies they won’t be accepted to make aliyah to Israel.”
The photo was taken in 2006 as part of a documentary project on Falashmura immigrants. Some of the photos from Koren’s collection appeared in an exhibition put on by the Jewish Agency.
In response to the uproar on Facebook, Koren – who claimed to receive threats and demands to remove the photo – took the picture off the Internet on Tuesday morning. He said he took the photo down not as a result of pressure, but out of concern for the safety of the photographed woman.
“All the furious reactions and threats don’t frighten me,” Koren told Haaretz. “I took the photo down after I understood that it could harm the woman. Let’s put everything into proportion, we live in a democratic country, where you can morally assess these things more than once. This whole thing kind of went out of control. I’m a documentarian whose whole life revolves around things that are on the edge.”
Koren added that he is willing to do everything for his journalistic integrity, and that since his subject matter is risqué and can appear provocative to some but not to others, he is not willing to apologize for it.
The Jewish Agency harshly condemned the “invasion of privacy” that resulted from the photo being taken and posted online. “Respect for human beings is more important than any piece of art or documentation,” said the agency, explaining that Koren went to Ethiopia in 2006 to document the immigration of a family to Israel. While he holds the exclusive rights to his pictures, some were donated to the Jewish Agency for an exhibition of some 40 photos that assisted in fundraising for the absorption of Ethiopian immigrants to Israel, the organization added.
“Needless to say, none of the pictures from the mikveh were developed nor displayed at the exhibition,” said the Jewish Agency, adding that it is important to note the organization only became responsible for the management of the camp, including the mikveh, in 2011. “At the time the photos were taken, the Jewish Agency was not responsible for the operations of the complex,” it said.
Rabbi Waldman, who is responsible for the field of Judaism at the complex, said he would not have allowed a photographer into the mikveh whilst there is a man or woman inside.

“የኢህአዴግ መሪዎች ገመና” ተስፋዬ ገ/አብ

10 Feb

የተከበሩት የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትር ጁነዲን ሳዶ አንድ ከባድ ችግር ገጥሞአቸዋል። ለማውራት እንኳ ይቀፋል። ግን ምን ይደረግ? ማን እየመራን እንዳለ ማወቅ ስለሚገባ መናገር አለብኝ። ሚኒስትሩ የፈፀሙት፣ ታዋቂው አክተር ሸዋዚንገር በሚስቱ ላይ ከፈፀመው ስለሚብስ፣ የሸዋዚንገርን ደግሞ በሜድያ ስለሰማን፣ ይህንንም የኛን ጉድ ልነግራችሁ ተገድጃለሁ። ደግሞም የተከበሩት ሚኒስትር ጁነዲን ሳዶ ምርጫ ካጭበረበሩ ወሮበሎች አንዱ በመሆናቸው ልናዝንላቸው አይገባም።
የሆነው ሆኖ ነገሩ እንዲህ ነው…
ከጥቂት ሳምንታት በፊት የተከበሩት ሚኒስትር ጁነዲን ሳዶ ሚስታቸው በሰላም ወለደች። በውነቱ አስደሳች ዜና ነበር።
የሚስታቸው ታናሽ እህት ደግሞ አራስ እህቷን ለመርዳት ሻንጣዋን ይዛ ከሚኒስትሩ ቤት ገባች። የተወለደችው ህፃን አንድ ሳምንት እንደሆናት፣ እኒህ ከፍተኛ የኢህአዴግ ባለስልጣን አንድ ያልተጠበቀ አስደንጋጭ ድርጊት ፈፀሙ።
እኩለ ሌሊት ላይ ወደ ሚስታቸው እህት የመኝታ ክፍል በመግባት አፏን አፍነው፣ ክብረ ንፅህናዋን ደፈሯት። ፈፅመው ሲያበቁም ለቀቋት። የመሰላቸው የሚስታቸው እህት “ውርደቷን ተሸክማ ፀጥ ትላላች” የሚል ነበር።
ሳይሆን ቀረ። እሪታዋን አቀለጠችው።
አራሷ ደንግጣ ከአልጋዋ ተነሳች። ታላቅ ግርግር ተፈጠረ። በመጨረሻ በተፈጠረው አለመግባባት አራሷ ህፃን ልጇንና እህቷን ይዛ ከቤት ወጣች። ሚኒስትሩ በተመቸው መኖሪያ ቤቱ ውስጥ፣ ከነምቾቱ ቀረ። የከሰሰውም የነካውም የለም። ስልጣኑን፣ ቤቱንና ንብረቱን እንደያዘ ቀጠለ።
አራሷ ይህ ጥቃት የተፈፀመባት በወለደች ልክ በአስራሶስተኛው ቀን ነበር። እነሆ! የኢህአዴጉ ከፍተኛ ባለስልጣን ከነ ክብሩ በስልጣኑ ላይ አለ። ሚስቱም ከነ ውርደቷ ተወርውራለች። ይህ ሁኔታ ለመለስ ዜናዊ ሪፖርት ተደርጎለታል። ጉዳዩ ወደ አደባባይ እንዳይወጣም መለስ ዜናዊ መመሪያ ሰጥቶበታል።
እስኪ የህግ ሰዎችና የሴቶች መብት ጉዳይ ተከራካሪዎች አስተያየት ስጡበት? በመሰረቱ እንዲህ ያለ ድርጊት የፈፀመ ሰው ሚኒስትር ሆኖ መቀጠል አለበት? መለስ ዜናዊስ ይህን ወንጀል ለመሸፋፈን መሞከሩ አያስጠይቀውም?

የአፍሪካ ኀብረት ዓለም በቃኝ ገባ

6 Feb


ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም
የዛሬ አርባ ዘጠኝ ዓመት ግድም በአፍሪካ አዳራሽ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት (የዛሬው የአፍሪካ ኀብረት) ሲመሠረት ተመልካች ሆኜ ገብቼ እዚያው አድሬአለሁ፤ የዛሬዎቹ ወጣቶች ያቺን ኢትዮጵያና እነዚያን ኢትዮጵያውያን የሚያውቋቸው አይመስለኝም፤ አንዳንዴ ሳስበው ግምትም ያላቸው አይመስለኝም፤ የነሱ ጥፋት አይደለም፤ ሥርዓት ባለው መንገድ ሥራዬ ብሎ፣ የአገር ጉዳይ ነው ብሎ ያስተላለፈላቸው የለም፤ ዛሬ የንክሩማ ሐውልት በአፍሪካ ኀብረት ግቢ ቆመ የሚል ወሬ ስሰማ ደርግ በአፍሪካ አዳራሽ መግቢያ ላይ የሌኒንን ሐውልት መትከሉን አስታወሰኝ፤ ዛሬ ደግሞ ወያኔ ከማን አንሼ ብሎ የንክሩማን ሐውልት በአፍሪካ ኀብረት ግቢ ውስጥ ተከለ፤ ንክሩማ ትልቅ አፍሪካዊ ነው፤ ነገር ግን ለአገሩም አልበቃም፤ በምንም ዓይነት መንገድ አጼ ኃይለ ሥላሴን አይተካም፤ ኢትዮጵያ ሰው አጥታ ከጋና መበደርዋ ኢትዮጵያ የወረደችበትን አዘቅት ያሳያል፤ እነማን ይዘዋት እንደወረዱም ግልጽ ነው፤ አንድ ሰው ብቻ፣ አጼ ኃይለ ሥላሴ፣ የተዋረዱ እንዳይመስለን፤ የተዋረደችው ኢትዮጵያ ናት፤ እንደተለመደው ጠምዝዘው ጋናን ማጣጣል ወይም የጋናን ክብር መቀነስ አድርገው የሚያቀርቡት ይኖሩ ይሆናሉ፤ የምለው ጋና ከኢትዮጵያ አትቀድምም፤ ንክሩማም ከአጼ ኃይለ ሥላሴ አይቀድምም ነው፤ ንክሩማም ቢኖር በአፍሪካ ኀብረት ጉዳይ ከአጼ ኃይለ ሥላሴ ጋር ለውድድር አይቀርብም ነበር፤ ጋና ነጻ በወጣችበት እለት በዓሉን ለማድመቅ የሄዱት ልዑል ሣህለ ሥላሴና አቶ አበበ ረታ ነበሩ፤ ከተመለሱ በኋላ አቶ አበበ በብሔራዊ ቤተ መጽሐፍት ስለጋና ንግግር አድርገው አዳምጫለሁ፤ ኢትዮጵያኮ በኢጣልያ ወረራ ጊዜም የአርበኞችዋን ነፍስ ይማርና ሰንደቅ ዓላማዋ ሲውለበለብባት የነበረች አገር ናት፤ የአርበኞችዋን ነፍስ ይማር! ሐውልት ባናሠራላቸውም ሲናቁብን በአርምሞ ልናልፈው አንችልም፡፡
አርበኞችን ወደዳር ማስወጣትና የሥልጣን ወንበሮችን በባንዳዎች ማስያዝ አጼ ኃይለ ሥላሴ የጀመሩት ቢሆንም ለልጅ ልጅ የሚተላለፍ የአገር ውርደት መሆን የለበትም፤
በቅርቡ ሪፖርተር በርእሰ አንቀጹ የሀሳብ ማጠራቀሚያ (ቲንክ ታንክ) በሚል ርእስ ጽፎ ነበር፤ ከሹሞቹ ውጭ ሰዎች መኖራቸውን፣ የማሰብ ችሎታ ያላቸው መሆኑን፣ ሀሳባቸውን የሚያዳምጥ መኖሩን ካላረጋገጥን ሀሳቦች ዋጋ የላቸውም፤ የንክሩማን ሐውልት በኢትዮጵያ ለመትከል ወይም የሌኒንን ሐውልት በኢትዮጵያ ለመትከል ከአንድ ሰው በቀር አይወስንም፡፡

የአፍሪካ አንድነት የተቋቋመው እ.ኤ.አ. በ1963ዓ.ም. ነው፤ በዚያን ጊዜ ኢትዮጵያ በመላው ዓለም ከፍ ያለና የተከበረ ስም ነበራት፤ በአፍሪካ ያለምንም ጥርጥር ቀዳሚዋ አገር ነበረች፤ ኢትዮጵያን ለዚህ ያበቃት ረጅም የነፃነት ታሪክዋ፣ የህዝቡ ጨዋነት፣ የመሪዎቹ፣ በተለይም የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ግርማና ሞገስ አንድ ላይ ሆነው ኢትዮጵያን የተከበረችና የተፈራች አገር አድርገዋት ነበር፡፡
ለአፍሪካ ኀብረት የተሰበሰቡት በዘመኑ የነበሩ ታላላቅ መሪዎች፣ አገሮቻቸውን ከቅኝ አገዛዝ ያወጡ ሰዎች ነበሩ፤ መሪዎቹ በየሰፈራቸው የጎረቤቶች መኀበር እያቋቋሙ ለትልቁ የአፍሪካ አንድነት እምብዛም ግድ አልነበራቸውም፤ ምናልባትም የአፍሪካ አንድነት ድርጅትን በማቋቋም እያንዳንዳቸው በየአገራቸው ያላቸው ሥልጣን የሚ¬¬¬-ቀነስባቸው መስሎአቸው የነበረ ይመስለኛል፤ አብዛኛዎቹ እናጥናው፣ እናብላላው በማለት የድርጅቱን ምሥረታ ለማስተላለፍ በፓም ይጥሩ ነበር፤ አጼ ኃይለ ሥላሴ ግን የድርጅቱ ሰነድ ሳይፈረም ማናችንም ከአዳራሹ አንወጣም ብለው ገትረው ያዙአቸው፡፡
የአጼ ኃይለ ሥላሴ ትልቅነትና የኢትዮጵያ የመንፈስ መሪነት በገሀድ ታየ፤ እንደናስርና እንደቤን ቤላ ያሉ አብዮተኞች ሳይቀሩ ከጃንሆይ ጋር ሲነጋገሩ ጎንበስ ብለውና እጆቻቸውን ወደኋላ አጣምረው ነበር፤ መቼም የዚህ ፊልም አንድ ቦታ ይኖራል ብዬ ተስፋ አለኝ፤ የዛሬ ወጣቶች ሁሉ ሊያዩት የሚገባ ነው፤ እምቢተኞቹንና አፈንጋጮቹን ሁሉ አንድ በአንድ እያነጋገሩ፣ እንደኒዬሬሪና አሚን ተጣልተው የማይነጋገሩትን እያስታረቁ ሰነዱ ሳይፈረም መውጣት የለም አሉ፤ እንደማስታውሰው ሰነዱ ከሌሊቱ በስምንትና በዘጠኝ መሀከል ተፈርሞ አለቀና ሲነጋ በየቤታችን ገባን፡፡
የአፍሪካ አንድነት በጋዳፊ (ነፍሱን ይማረውና) ውትወታ የአፍሪካ ኀብረት ተባለ፤ ስልቻ ቀልቀሎ፣ ቀልቀሎ ስልቻ ነው፤ ዓላማው የአፍሪካን ሕዝቦች የኑሮ ደረጃ ከፍ ለማድረግ፣ የአፍሪካ አገሮችን ሉዓላዊነትና ነጻነት ለመጠበቅና ከማናቸውም ዓይነት ቅኝ አገዛዝና ቄሣራዊ ተጽእኖ ለመከላከል ነበር፤ ነበር፤ ነበር፤ በአገሮች መሀከል የሚከሰቱ ችግሮችን ሁሉ በሰላማዊ መንገድ መፍትሔ እንዲገኝላቸው ማድረግ ነበር፤ ነበር፤ ነበር፡፡
እንደዚያ ዕለት በኢትዮጵያዊነቴ ኮርቼ አላውቅም፤ ስለዚህም የኢትዮጵያውያን የዩኒቨርስቲ መምህራን ማኀበር ስብሰባ ጠራሁና ያየሁትን ገልጬ ለአጼ ኃይለ ሥላሴ የምስጋና ደብዳቤ እንጻፍላቸው የሚል ሀሳብ አቀረብኩ፤ አንዳንድ ተቃውሞ ተነሥቶ ከተከራከርንበት በኋላ እንዲጻፍላቸው ተወሰነ፤ ዳብዳቤውን ጽፌ ለጃንሆይ እንዲሰጥልን ለዩኒቨርስቲው ፕሬዚደንት ለልጅ ካሣ ወልደማርያም አስረከብሁት፤ ከጥቂት ቀናት በኋላ ጠራኝና አንተው ወስደህ ብትሰጥ ይሻላል አለኝ፤ የምሄድበትን ቀንና ሰዓት ነገረኝ፤ ወስጄ በእጃቸው ሰጠኋቸው፤ እንዳነበቡት ወይም እንደተነበበላቸው ፍልቅልቅ ባለ ደስታቸው ይታይ ነበር፡፡
ዛሬ የአፍሪካ አንድነት (ኀብረት) በቻይና ቸርነት ፎቅ ተሠርቶለት ዓለም በቃኝ ገባ አሉ፤ የአፍሪካ መሪዎችም እዚያው ተሰበሰቡ፤ አቶ መለስም ለቻይና አስተዋጽኦ ዋጋ ለመክፈል ለማኦትሴ ቱንግ ተማሪ ሐውልት አስተከለ፤ ቀጥሎም የአፍሪካ መሪዎች በምን ምክንያት ወደ አውሮፓ ዓለም-አቀፍ ፍርድ ቤት ይሄዳሉ በማለት አቶ መለስ ተቆጥቶ በዓለም-በቃኝ ፎቅ ውስጥ የአፍሪካ ፍርድ ቤት ማቋቋም እንችላለን የሚል ሀሳብ አቀረበ ተባለ፤ ማን በማን ላይ እንዲፈርድ ይሆን? የአውሮፓ ዓለም-አቀፍ ፍርድ ቤት የተፈራው ምኑ ነው? ወይስ የዓለም-አቀፍ ትርጉም ችግር ሆኖ ነው? መቼም የአፍሪካ ፍርድ ቤት ዓለም-አቀፍ ደረጃ ላይ ይውጣ ማለት…ምን ማለት ይሆን? የተባበሩት መንግሥታትስ መቼ ነው ተለይቶ ‹‹አፍሪካዊ›› የሚሆነው?
ለማናቸውም በእግዚአብሔር መንግሥት ውስጥ ሆነው የሚመለከቱን የኢትዮጵያ አርበኞች ይቅር ይበሉን፤ ለኢትዮጵያም ከሌኒን ያወጣት አምላክ ያውቃል!

%d bloggers like this: