Archive | Religious RSS feed for this section

ዲስማስ፤ ነገር የገባው ሌባ፡

13 Apr

OLYMPUS DIGITAL CAMERA፡ ዲስማስ፤ ነገር የገባው ሌባ፡ በጆናስ ጆንታምቤክ ወደተላክንበት ሃይማኖታዊ ትምህርት ስንመለስም፤ የገባው፤ የሚለውን ቃል፤ አለቃ ታየ እንዴት እንደሚተረጉሙት ለጊዜው እንለፈውና፤ በነገራችን ላይ አለቃ ታየ; በ1899ዓ.ም. ፤ከአማርኛ፤ እና ግእዝ ፤ ሊህቅነታቸው ባሻገር፤ በጀርመን ዩኒቨርሲቲ ሌክቸረርና፤ በጀርመን፤ጣሊያን፤ እና ግሪክ፤ በነበራቸው እውቅና ከየመሪዎቹም ሜዳሊያዎችን የተረከቡ አዋቂ ናቸው፤፤(በዚህን ጊዜ ግማሹ ኢትዮጲያዊ እርግጥ ነው ከዛፍ ላይ አልወረደም ይሆናል)፤፤ በተለይ በሃመር አካባቢ እስከ 10 ኛው የአብየት በኣል ድረስ ፤እንደ አዳምና ሄዋን ቅጠላ ቃጠል ለባሽ ነበረ አሉ፤፤   አሁን የብሄር ብሄረሰቦች ልብስ የሚባለው ፤ የ10 ኛው አብዮት በአላችን የልብስ ህዳሴ ነበር ብሎ አንዱ ጸሃፊ አስኮምኮናል(አስኮምክሞናል)(የጎሳዬን ልብስ ጨምሮ መሆኑ ነው፤፤ ) ወደ ገደለው ስንመለስ፤ ይህ ጌዜ ከፋሲካ በአል ጋር ተያይዞ ስለሚነሳው ነገር የገባው ሌባ፤ ፈረንጆቹ ስላመለኩት (Penitent Thief) ትንሽ ብንል ምን ይለናል፤፤ ነገር የገባው ሌባ ወይም ንስሃ የገባው ሌባ፤ ጎሎጎታ ላይ በተጠቀማት መልካም አንደበት፤ ያለፈው ዲስማስ፤ በ18 ኛው ምህረተ ዘመንም ሃውልት የተሰራለት ብቸኛ ሌባ ሳይሆን አይቀርም(ሃውልቱም በቼክ ሪፐብሊክ፤ መስቀሉን ታቅፎ እንዲሆን ተደርጓል፤፤) ምን ባለሃውልት ብቻ የተዜመለት፤ የተቀኘለት እና ቅዱስ ለመባል የበቃም እንጂ፤፤ መፅሃፍ ቅዲስ ላይ ስማቸው ባይገለጽም፤ ያው፤ ስም ለመለያ አይደል፤፤ እስከ መቼ፡ ነገር የገባው ሌባ እና ነገር(ንስሃ) ያልገባው ሌባ እያልን ረጃጅም ቃላት እየተጠቀምን እንቀጥላለን በሚል ይመስላል፤ በ4ኛው ምህረተ ዘመን፤ የኒቆዲሞስ ወንጌል በሚባለው ገድል፤ ላይ ስማቸው እንዲወጣ ተደረገ፤፤ የኒቆዲሞስ ወንጌል፤ ብዙ አወዛጋቢ ነገሮችን የያዘ ቢሆንም፤ ስማቸው ያልተገለጡትን የመፃኅፍት ስሞች በማጋለጥ ተወዳዳሪ የለውም ይባላል፤፤ ዲስማስ ፤ ከክርስቶስ እየሱስ በስተቀኝ የተሰቀለው ሌባ ሲሆን፤ ጌስታስ ደግሞ ሌላኛው ሌባ መሆኑ ነው፤፤ በቀኝ ዋል የተባለው ሌባ አሁን ሌባው ዲስማስ ሳይሆን፤ ቅዱስ ዲስማስ በመባል ይታወቃል፤፤ ክርስቶስም አንገቱን ወደቀኝ አድርጎ የሞተው፤ ከዲስማስ ጋር አብሮነቱን ለማሳየት ነው ተብሏል፤፤ እናም ለቅዱስ ዲስማስ(በእለተ ቀኑ፤ ማርች 25)፤ በካቶሊክ እንዲህ ይፀለይለታል፤ ባለድሉ ቅዱስ ዲስማስ፤ አንተ እኮ በቀጥታ በክርስቶስ ተመርጠህ፤ የፃድቃን ዝርዝር ውስጥ የገባህ ነህ አንተ እኮ ከእሱ ጋር ገነት እንድትገባ የተወሰነልህ፤ በትክክለኛ የንስሃ ጥያቄህ ፤ በጎሎጎታ የፍርድ ማማ ላይ እውነተኛ ሃዘንህን አሳይተህ ከእሱ ጋር የተሰቀልክ አንተ፤ ከእነሱ ጦር ይልቅ በእውነተኛው ፍቅርህ፤ የእየሱስን ልብ ለንስሃና ፍቅር የከፈትክ፤የደህንነታችን እና የይቅር ባይነት መንገድ ከፋች አንተ፤ ከእየሱስ ጎን ሆነህ ፤ ህመሙን ስቃዩን ያየህ፤ መልካም ቃላትን በመጨረሻው ሰአት ከምትወደው እናቱ ማሪያም ይልቅ የሰጠህ አንተ፤ በትክክል እንዴት መጸለይ እንደሚቻል የምታውቅ፤ እባክህን ለእኛም ይቅርታና ፀጋን እንድናገኝ እርዳን፤አስተምረን አንተ፤በገነት ከእሱ ጋር ያለህ፤ በምድርም የመጨረሻው ሰአት አብረኸው የነበርክ፤ ከእሱ እንዳንለይ ፀልይልን፤ ይልቅም፤ በህይወቴ መጨረሻ ላንተ ያሰማህን መልካም ቃላት ያሰማን፤ እየሱስ፤ ጌታ ሆይ በመንግሰትህ አስበን ስንልህ፤ Jesus, Lord, remember me when thou comest into thy kingdom በዛሬዋ ቀን ከእኔ ጋር በገነት ትገባላችሁ፤በለን አሜን፤፤ Verily I say unto thee, Today shalt thou be with me in Paradise እንደ ዲስማስ፤ አጨራረሴን አሳምረው!!!!!!!!!!

Advertisements
%d bloggers like this: