“የኢህአዴግ መሪዎች ገመና” ተስፋዬ ገ/አብ

10 Feb

የተከበሩት የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትር ጁነዲን ሳዶ አንድ ከባድ ችግር ገጥሞአቸዋል። ለማውራት እንኳ ይቀፋል። ግን ምን ይደረግ? ማን እየመራን እንዳለ ማወቅ ስለሚገባ መናገር አለብኝ። ሚኒስትሩ የፈፀሙት፣ ታዋቂው አክተር ሸዋዚንገር በሚስቱ ላይ ከፈፀመው ስለሚብስ፣ የሸዋዚንገርን ደግሞ በሜድያ ስለሰማን፣ ይህንንም የኛን ጉድ ልነግራችሁ ተገድጃለሁ። ደግሞም የተከበሩት ሚኒስትር ጁነዲን ሳዶ ምርጫ ካጭበረበሩ ወሮበሎች አንዱ በመሆናቸው ልናዝንላቸው አይገባም።
የሆነው ሆኖ ነገሩ እንዲህ ነው…
ከጥቂት ሳምንታት በፊት የተከበሩት ሚኒስትር ጁነዲን ሳዶ ሚስታቸው በሰላም ወለደች። በውነቱ አስደሳች ዜና ነበር።
የሚስታቸው ታናሽ እህት ደግሞ አራስ እህቷን ለመርዳት ሻንጣዋን ይዛ ከሚኒስትሩ ቤት ገባች። የተወለደችው ህፃን አንድ ሳምንት እንደሆናት፣ እኒህ ከፍተኛ የኢህአዴግ ባለስልጣን አንድ ያልተጠበቀ አስደንጋጭ ድርጊት ፈፀሙ።
እኩለ ሌሊት ላይ ወደ ሚስታቸው እህት የመኝታ ክፍል በመግባት አፏን አፍነው፣ ክብረ ንፅህናዋን ደፈሯት። ፈፅመው ሲያበቁም ለቀቋት። የመሰላቸው የሚስታቸው እህት “ውርደቷን ተሸክማ ፀጥ ትላላች” የሚል ነበር።
ሳይሆን ቀረ። እሪታዋን አቀለጠችው።
አራሷ ደንግጣ ከአልጋዋ ተነሳች። ታላቅ ግርግር ተፈጠረ። በመጨረሻ በተፈጠረው አለመግባባት አራሷ ህፃን ልጇንና እህቷን ይዛ ከቤት ወጣች። ሚኒስትሩ በተመቸው መኖሪያ ቤቱ ውስጥ፣ ከነምቾቱ ቀረ። የከሰሰውም የነካውም የለም። ስልጣኑን፣ ቤቱንና ንብረቱን እንደያዘ ቀጠለ።
አራሷ ይህ ጥቃት የተፈፀመባት በወለደች ልክ በአስራሶስተኛው ቀን ነበር። እነሆ! የኢህአዴጉ ከፍተኛ ባለስልጣን ከነ ክብሩ በስልጣኑ ላይ አለ። ሚስቱም ከነ ውርደቷ ተወርውራለች። ይህ ሁኔታ ለመለስ ዜናዊ ሪፖርት ተደርጎለታል። ጉዳዩ ወደ አደባባይ እንዳይወጣም መለስ ዜናዊ መመሪያ ሰጥቶበታል።
እስኪ የህግ ሰዎችና የሴቶች መብት ጉዳይ ተከራካሪዎች አስተያየት ስጡበት? በመሰረቱ እንዲህ ያለ ድርጊት የፈፀመ ሰው ሚኒስትር ሆኖ መቀጠል አለበት? መለስ ዜናዊስ ይህን ወንጀል ለመሸፋፈን መሞከሩ አያስጠይቀውም?

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: