“ነፃ ስለሆንክ ይቅርታ አድርገን ወደ ቤትህ እንድትሄድ ፈቅደንልሀል አሉኝ” ደበበ እሸቱ /አርቲስትና ፖለቲከኛ/

21 Nov

For PDF file please click here: Debebe Eshetu

ማዕከላዊ የቆየሁት ሁለት ወር ከአምስት ቀን ግድም ነው። በዚህ ጊዜ ውስጥ
‹‹ቃል ስጥ›› በተባለው መሠረት ሰጥቻለሁ። የወገብ ዲስክ መንሸራተት ችግር ስላለብኝ
ቀዶ ጥገናም ስላደረግኩና ያመኝም ስለነበር አብዛኛውን ጊዜ ያሳለፍኩት ፖሊስ ሰራዊት
ሆስፒታል ነው። ሆስፒታል በማልሄድበት ጊዜ ቃል እየሰጠሁ ነበር። የፍ/ቤት ቀጠሮ
እየተራዘመ ሄደ። ለሦስት ጊዜያት ያህል ፍ/ቤት ቀርቤያለሁ። በስተመጨረሻ ግን ‹‹ጉዳዩን
አጣርተናል። መንግስት ደግሞ ሲጠረጥር ይይዛል። ሲፈለግና አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው
ይቅርታ ያደረጋልና በይቅርታው መሰረት ወደ ቤትህ መሄድ ትችላለህ›› አሉኝ። ‹‹እሺ›› ብዬ
ባለፈው ሳምንት አርብ ማታ ከቤተሰብዎቼ ጋር ተቀላቅያለሁ።

‹‹መንግስት ምህረት ያደርጋል›› አሉኝ ስትለኝ ጥርጣሬው እንዳለ ሆኖ ነው ምህረት
ያደረጉልህ ወይስ ከጥርጣሬው ነፃ ነህ ነው?ይህን ግልፅ ማድረግ ይቻል ይሆን?
እንደ ሚመስለኝ የሚጎዳ ሀሳብ፣ የሚጎዳ ድርጊት ስላልፈፀምኩ አጣርተን
ነፃ ስለሆንክ ይቅርታ አድርገን ወደ ቤትህ እንድትሄድ ፈቅደንልሀል ነው ያሉኝ።
የፍርድ ቤቱ ተደጋጋሚ ቀጠሮ ምን ምክንያት እየተሰጠው ነበር?
በቤት የተገኙ የተለያዩ ዶክመንቶችን እና ሲዲዎችን የማጣራት ነገር ነበር።
አንዳንዶቹም ይተረጎሙ ነበር። ብዙ ዶክመንት ነው ያለኝ። ከወረቀት እና ከመፃፍ ጋር ብዙ
ፍቅር አለኝ። ኢንተርኔት ውስጥም እገባለሁ። የሚመጡልኝ የኢ-ሜይል መልዕክቶች
አንዳንዶቹ ዶክመንቶች ሲሆኑ እየፃፍኩ ላለው መፅሐፍ ስለሚረዱኝ አልሰርዛቸውም፤
አስቀምጣቸዋለሁ። እነሱ ሁሉ መጣራት ስለነበረባቸው መርማሪው አልጨረስኩም ገና
ነኝ እያለ ያስረዳ ነበር።
አዋጁ [የፀረ-ሽብርተኝነት] በሽብርተኝነት የተጠረጠሩ ሰዎች ጉዳይ በአራት ወር ጊዜ
ውስጥ ተጣርቶ ማለቅ አለበት ስለሚል ረዥም ጊዜ የወሰዱት አዋጁን መሠረት አድርገው
ነው።
በአብዛኛው በአሸባሪነት የሚጠረጠር የፖለቲካ ተሳታፊ (ፖለቲከኛ) ነው። በአሁን
ሰዓት አንተ በየትኛው የፖለቲካ ፓርቲ ውስጥ ነው ያለኸው? [ይህን የጠየቅኩህ ከቅንጅት
በኋላ ነገሮች ስለተለዋወጡ ይህን የሚከታተሉ ስለ አንተ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ግልፅ የሆነ
ግንዛቤ እንዲያገኙ ብዬ ነው።]

በአሁን ሰዓት እኔ ከየትኛውም የፖለቲካ ድርጅት ጋር አይደለሁም። ያለፈውን
መፈረካከስ ውስጥ ‹‹ለምን ገባን?›› እያልኩ ስለማስበው እና ግራ ስለሚገባኝ የማንም
የፖለቲካ ድርጅት አባል አይደለሁም። በመጨረሻ የማነሳልህ ቅድም
‹‹የምፅፈው መፅሐፍ›› ብለህ ጠቀስ አድርገህ ነበር። የምትፅፈው ስለ ምንድን ነው? መቼስ
ይወጣል?

የእምነቴ ፈተና የሚል መፅሐፍ ፅፌ ነበር። አዲስ አበባ ውስጥ እና በእስሩ ወቅት
(በምርጫ 97 ሳቢያ) የነበረውን ሁላችንም ወደ ተመደብንበት የውጪ አገራት ስናመራ እኔ ወደ
አሜሪካ እና ካናዳ ሄጄ ነበር። የመጀመሪያው መፅሐፌ (የእምነቴ ፈተና) ካናዳ እስከሄድኩበት
ጊዜ ድረስ ሄዳ ትቆም ነበር። አሁን የምፅፈው እያለቀ ያለው መፅሐፍ ካናዳ ካሉ የቅንጅት
ደጋፊዎች እና እርዳታ አሰባሳቢ ኮሚቴ ቢሮዎች ጋር በመሆን እዚያ ላሉት የቅንጅት
ደጋፊዎች የሰጠኋቸውን መግለጫዎች እና የነበረውን ሁኔታ ያሳያል። አሜሪካ አገር
ያለውን ሁኔታም ያካትታል።

አሜሪካ እናንተ ተሰብስባችሁ ‹‹አንድ ምሽት ከደቤ ጋር›› በሚል ስለተዘጋጀው
ፕሮግራም፣ አዲስ አበባ ከተመለስኩ በኋላ ቅንጅት ቡዳ ከበላው በኋላ ለምን ወደዚያ
ደረጃ ደረሰ የሚለውን፣ የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት አባል ስለነበርኩ የአመራር አባላት፣
ሊቀ-መንበሮች፣ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አካላት ዲፕሎማሲያዊ በሆነ መልኩ ተናግረው
ያለፉትን ነገር ህዝብ ማወቅ ስላለበት ከማስታውሰው እና ከመዘገብኩት ቃለ-ጉባዔ
ጋር በማገናኘት እውነቱን ያሰፈርኩበት ነው።
መዝጊያ ቸግሮኝ ነበር አሁን አግኝቻለሁ። ስለዚህ መደምደሚያው የሚሆነው የእኔ
ማዕከላዊ ገብቶ መውጣት ነው።መፅሐፉን ለማንበብ ብዙ-ሰው
የሚቸኩል ይመስለኛል።

እግዜር ይስጥልኝአመሰግናለሁ

Source: The last edition of Awramba Times

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: