ፋራ

17 Aug

Extracted from this PDF file, here: https://jontambek.files.wordpress.com/2011/08/pdf-file.pdf

በያሬድ አይቼህ

ግንቦት 7 ፡ ኦነግ (OLF) እና ኦህነግ (ONLF) ላለፉት ጥቂት ወራት ውይይት ላይ እንደሆኑ ተናግረዋል። ውይይት መልካም ነው። በተለያዩ ከተሞች እስካሁን ከዲያስፓራ ማህበረሰብ ጋር ያደረጉትን ውይይቶች ተከታትያለሁ። ምናልባት ከአንድ ከተማ ወደ ሌላ ከተማ የውይይታቸው መሰረታዊ ነጥብ ያድጋል ይሻሻላል የሚል ግምት ነበረኝ። እንኳንስ ሊያድግ እና ሊዳብር ፡ የኦነግ እና የኦህነግ አላማ ያው መገንጠል እንደሆነ ነው የቀጠለው። ለመሆኑ ግንቦት 7 ከነዚህ ወገኖቻችን ጋር የሚያደርገው ውይይት ዲያስፖራውን ቀስ በቀስ ለማደንዘዝ ብሎ ነውን? ከሆነ የእኔ መልስ “እምቢ አልደነዝዝም!” ነው።
የኦነግ ፡ የኦህነግንም ሆነ የግንቦት7ን ደጋፊዎች አከብራቸዋለሁ ፤ እንደ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ እወዳቸዋለሁ። ኦነግን ግን የማየው እንደ ፋራ ድርጅት ነው። ይህን ስል በስደብ መልኩ ማለቴ አይደለም።
የኦነግ የአደባባይ ገፅታ (public image) በጣም ፋራ የሆነ ድርጅት መሆኑን ለመመልከት አቶ ሌንጮ ለታ በኢሳት ቲቪ1 ላይ አንድ ጊዜ በእንግሊዝኛ በሰጡት ቃለምልልስ ላይ በቀላሉ መመልከት ይቻላል ፤
ጋዜጠኛው በአማርኛ ይጠይቃቸዋል እሳቸው በእንግሊዝኛ ይመልሳሉ። (አቶ ሌንጮ አማርኛ አቀላጥፈው መናገር ይችላሉ።) እንዲሁም ከዚህ ቃለ ምልልስና ከሌሎችም የኦነግ ደጋፊዎች እንደተረዳሁት ከሆነ የኦነግ
ትግሉ ከአፄ ምንሊክ ጋር ይመስላል።
አፄ ምኒሊክ ጋር እንዴት መታገል ይቻላል? ሞተዋል እኮ! በስትሮክ (stroke) ነው የሞቱን የሚል ፅሁፍ አንብቤያለሁ። ኦነግ ግን የአፄ ምንሊክ ነገር ነው የሚያንገበግበው ። ይህ ዝንባሌው ስለፖለቲካ
መሰረታዊ ምንነት አያቅም ወይ የሚል ጥያቄ በተደጋጋሚ እንዲነሳብኝ አድርጓል። ፖለቲካ ስለ አሁን ፡ ወደፊት እና ስለ ጥቅም ነው። አፄ ምንሊክ ጋር የሚታገል ድርጅት አሁን ያለውን የአገራችንን የፖለቲካና
የኢኮኖሚ ተግዳሮቶችን (challenges) መጋፈጥ የሚችል ድርጅት መሆኑ አጠያያቂ ነው።
በተጨማሪ ፡ ኦነግ የፖለቲካ ትግል ስልቱ መራቀቅ (sophistication) የሚጎለው ሆኖ ይሰማኛል።
ለምሳሌ የኦነግ አንዳነድ አባሎቹ ኦሮሞ ላልሆኑ ኢትዮጵያውያን ሰላምታ መንፈጋቸው በጣም ያስገርመኛል። ምን አይነት ትግል መሆኑ ነው? ሰውን ሰላም ባለማለት ምን ለማግኘት ነው? ያውም እኮ ዲያስፖራ ነው የምንኖረው ፡ ኦሮሚያ ያለችው ኢትዮጵያ ውስጥ ነው። እባካችሁ ፡ የኦነግ አባላት ፡ ይህን አይነት ድርጊታችሁን አስቡበት ፡ ፋይዳ የለውም። እንዲሁም አማርኛ እያወቃችሁ በእንግሊዝኛ ሰላም የምትሉ ኦነጎች እንዳላችሁ ገጥሞኝ ያቃል ፤ አማርኛ እያወቁ አልናገርም ማለት ፋራነት
ነው።

Interview with Lencho Letta

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: