ሰማያዊ ፓርቲ

26 Jul

ብዙ ዘመን ሰላምን፤ ብዙ ዘመን አንድነትን፤ ብዙ ዘመን ተስፋን ናፍቀናል ሰማያዊ ቀለም ደግሞ እነዚህን ናፍቆቶች ሁሉ አቅፏል፡፡ ሰማያዊ ማለት ሰላም አንድነትና ተስፋ ማለት ነው፡፡ “ኢትዮጵያን ለኢትዮጵያውያን” መልሰው ሊያስረክቡ በወሰኑ ወጣቶችና ሴቶች መሠረቱ ተጥሏል፡፡
ዓላማ
የሰማያዊ ፓርቲ ጥያቄ የኢትዮጵያ ሕዝብ ጥያቄ ነው፡፡ ኢኮኖሚያዊ ፖለቲካዊና ማሕበራዊ ጥያቄዎቻችን ሁሉ በሰላም በአንድነትና በተስፋ ውስጥ ይመለሳሉ ብሎ ሰማያዊ ፓርቲ ያምናል፡፡ ክፉን በክፉ ሳይሆን ክፉን በመልካም ድል በመንሳት የአገራችንን ፖለቲካ ከሴራ ከጥላቻና ከመጠላለፍ ያወጣል በምትኩ የሀሳብ ልዕልና የሚነግስበት፤ ልዩነት የሚከበርበት ፓርቲ ይሆናል፡፡ ክርክር ውይይትና የሀሳብ ፍጭት የፓርቲው የማዕዘን ድንጋዮች ናቸው፡፡፡
አዲስ አመለካከት መፍጠር የዘወትር የቤት ሥራችን ነው፡፡አዲስ ሥርዓት የሚመሰረተው በመጀመሪያ አዲስ አመለካከት ሲፈጠር ነውና፡፡ እናም ኢሕአዴግን በመቃወም ብቻ ሳይሆን ኢሕአዴግንም ጭምር ነፃ በማውጣት ነው፡፡
ፍርሀትን፤ ጥርጣሬን ፤ በቀልን፤ መለያየትን ከእግራችን በታች የምናውለው ለአስተሳሰብ ለውጥ ራሳችንን ባስገዛን መጠን ነው፡፡

ኑ ራሳችንን ነፃ በማውጣት የአገራችንን ዕጣ ፈንታ እንወስን!

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: